Popular Posts

Monday, April 2, 2018

ባህሪ ይጠይቃል

ችሎታህ ወደ ላይ ላይ ሊወስድህ ይችላል፡፡ ነገር ግን እዚያ ለመቆየት ባህሪ ይጠይቃል፡፡
ተሰጥኦው በርን ከፍቶ ያስገባሃል፡፡ ነገር ግን ባህሪ በክፍሉ ውስጥ ያቆይሃል፡፡
ስጦታህ ባህሪህ አንተን መጠበቅ የማይችልበት ቦታ ቢወስድህ ዋጋ የለውም፡፡
በህይወት ለመሳካት ስጦታ ይጠይቃል ባህሪም ይጠይቃል፡፡
በህይወት ለመከናወን የተከፈተ እድል ይጠይቃል ባህሪም ይጠይቃል፡፡
በህይወት ለመሳካት ተሰጥኦ ይጠይቃል ባህሪም ይጠይቃል፡፡
በህይወት ለመከናወን ስጦታ የራሱ ድርሻ አለው ባህሪም የራሱ ድርሻ አለው፡፡
በህይወት ለመከናወን ስጦታ የሚሰራውን ባህሪ አይሰራውም ባህሪ የሚሰራውን ስጦታ አይሰራውም፡፡
በህይወት ለመከናወን ስጦታ ብቻ በቂ አይደለም፡፡
በህይወት ያነሰ ስጦታ ያላቸው ሰዎች ይበልጥ ሲከናወንላቸው ይታያል፡፡ በህይወት የበለጠ ክህሎት ያላቸው ሰዎች በባህሪ ማነስ ምክኒያት እንደሚገባው ሳይከናወልናቸው ይታያል፡፡
ስጦታን እኛ አንወስነውም፡፡ ተሰጥኦ ከእግዚአብሄር በስጦታ የሚሰጥ እንጂ ስጦታው እንዲሰጥ የሚደረግ ምንም አስተዋፅኦ የለም፡፡
ስጦታ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ አይነቱና መጠኑ ይለያይ እንጂ ስጦታ የሌለው ሰው የለም፡፡
ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። ማቴዎስ 25፡15
ስጦታ አለን ማለት በህይወት ይከናወንልናል ማለት ግን አይደለም፡፡ በህይወት እንዲከናወንልን ስጦታ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ እንዲሳካልን ከስጦታ ጋር ባህሪ ያስፈልገናል፡፡ እንዲያውም ስጦታውን የሚይዝ ባህሪ ከሌለን ስጦታው ከንቱ ነው፡፡ ስጦታውን ለመያዝ ባህሪን በትጋት ካላዳበርን ስጦታው ለማንም አይጠቅምም፡፡
ስጦታም ክህሎትም ተሰጥኦም የሚሰጠው ለሰው ጥቅም ነው፡፡ ከሰው ጋር እንዴት እንደምንኖር ካላወቅንና ባህሪው ከሌለን ስጦታው ለምንም አይጠቅመንም፡፡ ሁኔታዎችን እንዴት እንደምናልፍ የትግስት ባህሪ ከሌለን ስጦታው ከንቱ ነው፡፡ የመከራን ጊዜ እንዴት እንድምናሳልፍ ትህትናን ካላዳበርን ምንም አይጠቅመንም፡፡
በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው። ምሳሌ 24፡10
ባህሪ የሌለው ስጦታ ማለት ዘይትን ቀዳዳ እቃ ውሰጥ እንደማስቀመጥ ያህል ብክነት ነው፡፡ ባህሪ ስጦታውን በሚገባ እንድንጠቀምበት ያስችለናል፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ፍቅር #ሰላም #ስጋ #ምኞት #ማሰብ #ህይወት #ሞት #ደስታ #ዘር #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #ትህትና

No comments:

Post a Comment