Popular Posts

Sunday, April 8, 2018

በዚህም በዚያም ወደፊት እንሄዳለን

የእግዚአብሄር አሰራር ልዩ ልዩ ነው፡፡ ወደ እግዚአብሄር እንፀልያለን ምሪትን እንጠይቃለን፡፡ እግዚአብሄርን በአንድ መንገድ ብቻ አንጠብቀውም፡፡ ለእግዚአብሄር አሰራር ልባችንን እናሰፋለን፡፡ እግዚአብሄር ከዚህ በፊት በህይወታችን በሰራበት መንገድ ብቻ አንጠብቀውም፡፡
እግዚአብሄር ሁሉን ለራሱ አላማ ሊያስገዛ የሚችል የራሱ አሰራር አለው፡፡ እግዚአብሄር ሁሉን ለራሱ አላማ ሊያስገዛ የሚችልበት አሰራሩን ተከትለን በዚያ አሰራር ተመርተን ከእግዚአብሄር ጋር አብረን እንሰራለን፡፡  
የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡9
አንዳንዴ እግዚአብሄር ተራራውን እንደሚያነሳው ይናገረናል፡፡ እግዚአብሄር ተራራውን እንደሚያነሳው ሲመራን በንግግራችን ወይም በድርጊታችን ተራራውን ለማንሳት ይጠቀምብናል፡፡
እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡23
እግዚአብሄር ራሱ ተራራውን እንደሚያነሳው ሲናገረን ተራራውን እስኪያነሳው እንድንታገስ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡
ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ምንድር ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎችም፦ ሞገስ፥ ሞገስ ይሁንለት ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል ብሎ ተናገረኝ። ዘካርያስ 4፡7
ሌላ ጊዜ ደግሞ ተራራው እያለ እንዴት እንድምንወጣው ያሳየናል፡፡ እግዚአብሄር ተራራውን እንድንወጣው ሲመራን ተራራውን የምንወጣበትን ፀጋን ይሰጠናል፡፡
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9
በዚህም ሆነ በዚያ ወደፊት እንሄዳለን፡፡ በዚህም ሆነ በዚያ እግዚአብሄር በህይወታችን ያለውን አላማ እንፈፅማለን፡፡
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሮሜ 8፡35-37
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #ተራራ #ፀጋ #አላማ #የክርስቶስፍቅር #ስር #መሰረት #ትእዛዝ #መስጠት #ሃሳብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #መውደድ #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment