Popular Posts

Wednesday, April 4, 2018

ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት

ሰው የተሰራው በእግዚአብሄር በማረፍ እንዲሰራ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው መጀመሪያ እንዲያርፍ ከዚያም እንዲተጋ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በእረፍት እንዲሰራ እንዲተጋ ነው፡፡
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ። መክብብ 9፡10
የጉልበት ማጠራቀሚያ የለውም፡፡ ጉልበታችንን ባንጠቀምበት አይጠራቀምም፡፡ ጉልበታችንን ካልተጠቀምነበት እየበዛ ሳይሆን እያነሰ ነው የሚሄደው፡፡
ትንሽ ሰርቶ ትንሽ ከመኖር ብዙ ሰርቶ ብዙ መኖር ይሻላል፡፡ ትንሽ ሰርቶ ጉልበትን ጊዜንና አቅምን ከመፍጀት በደንብ መስራት በደንብ መኖር ይሻላል፡፡ በትንሽ ሰርቶ በትንሽ ከመኖር በደንብ ሰርቶ በደንብ መኖር ይሻላል፡፡
የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፤ የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች። ምሳሌ 10፡4
በአለም ላይ ትልቅ አቅም አለ፡፡ በከርሰ ምድር ውስጥ ብዙ ሃብት አለ፡፡ ለሰው ልጆች ሁሉ የሚበቃ ሃብት በምድር ውስጥ አለ፡፡ ነገር ግን ትጋትን ካላሳየን በስተቀር ያንን ሃብት ማግኘት አንችልም፡፡
አለም የሃብት ችግር ኖሮባት አታውቅም፡፡ አለም የትጋት እና የታማኝነት ችግር እንጂ የሃብት ችግር የለባትም፡፡ በአለም ላይ ለአለም ህዝብ ሁሉ የሚበቃ ብዙ አንጡረ ሃብት አለ፡፡ አለም በሃብት የተሞላች ነች፡፡ ያንን ሃብት ግን ማውጣት የሚችለው ትጉህ ሰው ብቻ ነው፡፡ ሰነፍ ሃብቱ አጠገቡ እያለ ሳያየው ሳይጠቀምበት በችግር ይሞታል፡፡  
ታካች ሰው አደን ምንም አያድንም፤ ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው። ምሳሌ 12፡27
አለም አገልግሎትን የተጠማች ነች፡፡ የሚያገለግላት ሰው ከተገኘ አለም ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኛ ነች፡፡ አለም የመክፈል ችግር የለባትም፡፡ አለም የማትፈልገው ሳይተጋ ሳይለፋ መጠቀም ብቻ የሚፈልገውን ሰው ነው፡፡ አለም ሳይሰራ ሳያገለግል ሳይለፋ የሚገለገልባትን ሰው አትፈልግም፡፡ አለም የምትፈልገው በታማኝነት የሚያገለግላትን ሰው ነው፡፡ በታማኝነት የሚያገለግላት ትጉህ ሰው ካገኘች አለም የሚያስፈልገውን ትከፍላለች፡፡
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ። መክብብ 910
ለመስራት ለመድከም ምድር ወርቃማ እድል አዘጋጅታለች፡፡ ሰው ሲሞት በመቃብር ይህንን የመስራት የመትጋት የማገልገል አድል ያገኘውም፡፡ ይህ እድል በምድር ላይ ላሉ ሰዎች ብቻ የተሰጠ እድል ነው፡፡
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል ጉልበታችን አንጠፍጥፈን የሰው ልጆችን እንድናገለግል ተጠርተናል፡፡  
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ትጋት #ስራ #መድከም #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትህትና #ልብ #እምነት

No comments:

Post a Comment