Popular Posts

Friday, April 6, 2018

የትልቅ እምነት ስልጣን

ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ሄደ። አሁንም ወደ ቤቱ በቀረበ ጊዜ የመቶው አለቃ ወዳጆቹን ወደ እርሱ ላከ፤ አለውም፦ ጌታ ሆይ በቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝምና አትድከም፤ ስለዚህም ወደ አንተ ልመጣ እንዲገባኝ ሰውነቴን አልቈጠርሁትም፤ ነገር ግን ቃል ተናገር፥ ብላቴናዬም ይፈወሳል።እኔ ደግሞ ከሌሎች በታች የምገዛ ሰው ነኝ፥ ከእኔም በታች ወታደሮች አሉኝ፥ አንዱንም፦ ሂድ ብለው ይሄዳል፥ ሌላውንም፦ ብለው ይመጣል፥ ባሪያዬንም፦ ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል። ኢየሱስም ይህን ሰምቶ በእርሱ ተደነቀ፥ ዘወርም ብሎ ለተከተሉት ሕዝብ፦ እላችኋለሁ፥ በእስራኤልስ እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም አላቸው። ሉቃስ 7፡6-9
ለስልጣን ንቁ የሆነን ሰው አሳዩኝ እምነት ያለውን ሰው አሳያችሁዋለሁ፡፡ የዚህ ፅሁፍ ፀሃፊ በህይወቱ በእምነታቸው ከተደነቀባቸው ሰዎች መካከል ለስልጣን ንቁ ያልሆነን ሰው አይቶ አያውቅም፡፡ የእምነት ሰዎች በሙሉ ለስልጣን ያላቸው ግንዛቤና አክብሮት ልዩ ነው፡፡ የእምነት ሰዎች በየደረሱበርት ቦታ እዚያ ላለው ስልጣን ራሳቸውን ይሰጣሉ፡፡
ትንሹም በታላቁ እንዲባረክ ክርክር የሌለበት ነገር ነው። ዕብራውያን 7፡7
ለስልጣን ንቁ የሆነን ሰው ማለት በደረሰበት ቦታ ሁሉ ላው ስልጣን የሚገዛ ሰው ማለት ነው፡፡ ለስልጣን ንቁ የሆነ ሰው ማለት አለም በስርአት እንደምትተዳደር የተረዳ ሰው ማለት ነው፡፡ ለስልጣን ንቁ የሆነ ሰው ማለት ሰው የሚባረከው ያንን ስልጣን ሲከተል ብቻ መሆኑን የተረዳ ሰው ማለት ነው፡፡ ለስልጣን ንቁ የሆነ ሰው ማለት እግዚአብሄር የሚባርከው በስርአት መሆኑን የተረዳ ሰው ማለይ ነው፡፡ ለስልጣን ንቁ የሆነ ሰው ማለት የእግዚአብሄርን አሰራር የተረዳ ሰው ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ። ሮሜ  13፡2
ሰው ስልጣን እንዴት እንደሚሰራ ካልተረዳ የእግዚአብሄር ቃል ስልጣን እንዴት እንደሚሰራ ሊረዳ አይችልም፡፡
ብላቴናዬ ሽባ ሆኖ እጅግ እየተሣቀየ በቤት ተኝቶአል ብሎ ለመነው። ኢየሱስም፦ እኔ መጥቼ እፈውሰዋለሁ አለው። የመቶ አለቃውም መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ በቤቴ ጣራ ከታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፥ ብላቴናዬም ይፈወሳል።እኔ ደግሞ ለሌሎች ተገዥ ነኝና፥ ከእኔም በታች ጭፍራ አለኝ፤ አንዱንም፦ ሂድ ብለው ይሄዳል፥ ሌላውንም፦ ብለው ይመጣል፥ ባሪያዬንም፦ ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል አለው። ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም። ማቴዎስ 8፡6-10
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ስልጣን #መረዳት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ዋጋ #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment