Popular Posts

Tuesday, April 24, 2018

እግዚአብሔር ታላቅ

እግዚአብሔር ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፤ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነው። 1ኛ ዜና መዋዕል 16:25
እግዚአብሔር ትልቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰ ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው። መዝሙር 48:1
አባታችን አግዚአብሄር ትልቅ ነው፡፡
እግዚአብሄር ትልቅ ብቻ ሳይሆን ለታላቅነቱም ፍጻሜ የለውም፡፡ እግዚአብሄር ታላቅ ነው የምንለው ታላቅ ወንድም እንደምንለው ከታናሽ ወንድም ጋር አስተያይተን አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ታላቅ ነው የምንለው ከሌላ የምንገልፅበት ቃል ስለሌለን ነው፡፡
እግዚአብሔር ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፤ ለታላቅነቱም ፍጻሜ የለውም። ትውልደ ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፥ ኃይልህንም ያወራሉ። መዝሙር 145፡3-4
እግዚአብሄርን እናምነዋለን እንጂ እግዚአብሄር እጅግ ታላቅ ስለሆነ በፍጥረት አቅም ተረድተን አንጨርሰውም፡፡
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 40፡28
መፅሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄር ታላቅ ነው እኛም አናውቀውም የሚለው እግዚአብሄርን አውቀን ስለማንጨርስ ነው፡፡
እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። ኢዮብ 36፡26
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መኖሪያህእግዚአብሄር #እግዚአብሄርታላቅ #እውቀት #ጥበብ #ሃይል #አይመረመርም #አልፋ #ኦሜጋ #መጀመሪያ #መጨረሻ #ክርስትያን #አማርኛ #መደገፍ #ማስተዋል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #ፅድቅ #ማመን #አምባ #ስልጣን

No comments:

Post a Comment