Popular Posts

Tuesday, April 17, 2018

ግፈኞች

ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። ማቴዎስ 11፡12
ሰይጣን የህይወት ጠላት ነው፡፡ ሰይጣን የሚመጣው ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ነው፡፡
ሰይጣን የዚህ አለም ገዢ ነው፡፡
ኢየሱስ በምድር ላይ የተመላለሰው የዲያቢሎስን ስራ ሊያፈርስ ነው፡፡
የዲያቢሎስን ስራ ሊያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ 1ኛ ዮሀንስ 3:8
እኛም በምድር ላይ ያለነው የዲያቢሎስን ስራ ለማፍረስ ነው፡፡
ኢየሱስም ዳግመኛ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው። ዮሃንስ 20፡21
ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤ ዮሃንስ 17፡18
በምድር ላይ ያለነው የእግዚአብሄር ፈቃድ በሰማይ እንዳለ በምድር ለማስፈፀም ነው፡፡
ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ ማቴዎስ 6፡10
የዲያቢሎስን ስራ ስናፈርስ ሰይጣን ዝም ብሎ አይመለከተንም፡፡ ስራውን ማፍረሳችንን ሰይጣን በእሺታ አያልፈውም፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ ከመስራት ሊያስቆመን ሰይጣን የቻለውን ሁሉ ይሞክራል፡፡
በምድር ላየ የምንኖረው ሰይጣን ስለፈቀደለን አይደለም፡፡ በምድር ላይ የእግዚአብሄርን መንግስት የምናስፋፋው ሰይጣን አዝኖልን ፈቅዶልን አይደለም፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ የምንሰራወ ከሰይጣን ጋር ተደራድረን አይደለም፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ በምድር ላይ የምንሰራው ሰይጣን ሳይወድ በግድ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምንፈፅመው በሃይል እና በስልጣን ነው፡፡
ሰይጣን ቢችል ያስቆመናል፡፡ ሰይጣን ቢችል ምንም ነገር በምድር ላይ እንድንሰራ አይፈቅድልንም ነበር፡፡
ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። ማቴዎስ 11፡12
የእግዚአብሄር መንግስት በምድር የምትሰራው ስላልተገፋች አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በምድር ያለችው ሁሉ ነገር ተመቻችቶላት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በምድር ያለችው በግድ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት በምድር ላይ የምትገዛው በሃይልና በስልጣን ነው፡፡   
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መንግስት #ሃይል #ስልጣን #ግፈኞች #ይናጠቋታል #ትገፋለች #ፈቃድ #እምነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ህብረት #ግንኙነት #ሽቱ #ያማረ #በፍፁምሃይል #መውደድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment