Popular Posts

Tuesday, January 2, 2018

የአባትና የልጅ እንቆቅልሽ ታሪክ

ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡33
ሰው ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥሮአል፡፡ ለእግዚአብሄር ክብር የተፈጠረው ሰው ለእግዚአሄር ክብር እሰከኖረ ደርስ ነገሮች ሁሉ ትክክለኛ ቦታቸውን ይይዛሉ፡፡ ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው የእግዚአብሄርን ነገር እንዲያስቀድም ነው፡፡
ሰው ማስቀደም ያለበትን የእግዚአብሄርን ነገር ሳያስቀድም የራሱን ነገር ሊያስቀድም ሲሞክር ሁሉም ነገሮች ቦታቸውን ይለቃሉ፡፡ሸ ሰው ግን ማስቀደም ያለበትን የእግዚአብሄርን ነገር ሲያስቀድም ሁሉም ነገሮች ቦታቸውን ይይዛሉ፡፡
የሰው ሃላፊነት ነገሮችን ቦታ ማስያዝ አይደለም፡፡ የሰው ሃላፊነት ለእግዚአብሄ ቅድሚያ መሰጠት ነው፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ቅድሚያ ከሰጠ ለሌሎችነገሮች ቅደም ተከተል መስጠት አይጠበቅበትም፡፡ ሰው ግን ለእግዚአብሄር ቅድሚየ ካልሰጠ የሚከረሉትን ነገሮች ሁሉ ቅደም ተከተል መስጠት አለበት፡፡
አንድ ጊዜ እንዲህ ሆነ አሉ፡፡ አንድ አባት በማንበቢያ ክፍሉ ውስጥ ሆኖ ተመስጦ መፅሃፍ ያነባል፡፡ ልጁ ደግሞ የአባቱን ትኩረት ፈልጎ ጥያቄ በመጠየቅ በተከታታይ ከተመሰጠበት ንባቡ ያቋርጠዋል፡፡
አባትም ልጁን ባተሌ የሚያደርግበት እና መፅሃፉን ተመስጦ የሚያነበብበት እንድ ብልሃት አገኘ፡፡ ለልጁ የተገዛለትን ፐዝል ብትንትን ካደረገው በኋላ ገጣጥመው ብሎ ለልጁ ይሰጠዋል፡፡ ልጁ ግን ፐዝሉን ጥቂት ደቂቃ ውሰጥ ገጣጥሞት ተመለሰ፡፡ አባትየው በልጁ ብልሃት እጅግ ሲገረም ልጁ ፐዝሉን መገጣጠም ቀላል እንደነበረ አስረዳው፡፡ ውስብስቡን ፐዝል ለመገጣጠም መቸገር እንደሌለበት ይልቁንም ከኋላ ያለውን የሰውን ምስል ማየትና የጀርባውን የሰው ምስል በመከተል ብቻ የፊቱን ፐዝሉን ሳያይ በትክክል መገጣጠም እንደቻለ ለአባቱ አስረዳ፡፡
እኛም ብዙ ጊዜ የምናተኩረው የህይወትን ችግሮችን በመፍታት ላይ ነው፡፡ የህይወትን ችግሮች የመፍታት ቁልፉ ያለው ለእግዚአብሄር ቅድሚያ በመስጠት ላይ ነው፡፡ ሰው ለእግዚአብሄር ቅድሚያ ከሰጠ በተዘዋዋሪ የህይወት ችግሮችን ቁልፍ እያገኘ ነው፡፡ ሰው ግን ለእግዚአብሄር ቅድሚያ ካልሰጠ የህይወትን ተግዳሮት ቁልፍ እየራቀው ነው፡፡
ሰው ውስብስብ ነገሮችን ከማወቁ በፊት የጥበብ መጀመሪያ ለሆነው ለእግዚአብሄር መፍራት ቅድሚያ መስጠት አለበት፡፡
ሰው ብዙ የሆነውን የህይወትን ሸክም ከመሸከሙ በፊት አስቀድሞ የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን መፈለግ አለበት፡፡
ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡33
ሰው ለብዙ ነገር ጥብበኛ ከመሆኑ በፊት ለወንጌል መልእክት ሞኝ መሆን አለበት፡፡ ሰው በራሱ መንገድ ለመዳን ከመሞከሩ በፊት ነፃ ስጦታ የሆነውን የእግዚአብሄርን ፀጋ መቀበል አለበት፡፡
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡18
ሰው በህይወቱ በራሱ ማስተዋል ከመደገፉ በፊት በመንገዱ ሁሉ እርሱን ማወቅ አለበት፡፡
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። ምሳሌ 3፡5-6
በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና። ሮሜ 8፡2
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#አትጨነቁ #ቅድሚያ ##እግዚአብሄርንመፍራት #ጥበብ #መንፈስ #ሞኝነት #የእግዚአብሄርን #እምነት #ምንእንበላለን #ምንእንጠጣለን #ምንእንለብሳለን #አስቀድማችሁ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment