Popular Posts

Saturday, October 14, 2017

የእግዚአብሔር የምድር መሠረቶች

አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር ይውጣ። ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡3 እና 8
እግዚአብሄር ምድርን ፈጥሮ አልተወውም፡፡ እግዚአብሄር በትጋት ምድርን እያስተዳደረ ነው፡፡ እግዚአብሄር በጥበቡና በሃይሉ በፍቅር እንደ እርሱ ነፃ ፈቃድ ያለው ሰው እየመራ ነው፡፡ ሁሉን ነገር ሞክረን መጨረሻ ላይ የሚሆነው የእግዚአብሄር ሃሳብ ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈለገውን ነገር በምድር ላይ ያደርጋል፡፡ ቁልፉ ያለው በእግዚአብሄር እጅ ነው፡፡  
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። መክብብ 9፡11
እግዚአብሄር ምስኪኑን ፣ ጉልበት የሌለውንና አቅም ያነሰውን ከመሬት በማንሳት ይታወቃል፡፡
በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19፡21
እግዚአብሄር የምድር ባለቤት ነው፡፡ እግዚአብሄር በሰዎች ጉዳይ ጣልቃ ይገባል፡፡ እግዚአብሄር ምንም የሆነውን ሰው ከፍ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሄር ችግረኛውን ከመሬት አንስቶ የክብር ዙፋን ያወርሰዋል፡፡
ልዑሉ በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለወደደውም እንዲሰጠው፥ ከሰውም የተዋረደውን እንዲሾምበት ሕያዋን ያውቁ ዘንድ ይህ ነገር የጠባቂዎች ትእዛዝ፥ ይህም ፍርድ የቅዱሳን ቃል ነው። ዳንኤል 4፡17
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ትህትና #መዋረድ #ባለቤት #ዝቅታ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #አዋቂ ####ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment