Popular Posts

Friday, September 8, 2017

ግብዣ ባደረግህ ጊዜ

የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው፦ ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትም እንዳይመልሱልህ፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ባለ ጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ። ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና። ሉቃስ 14፡12-14
የእግዚአብሔር መንግስት አሰራርና የአለም አሰራር እጅግ ይለያያሉ፡፡ የእግዚአብሔር መንግስትና የአለም አሰራር እጅግ ተቃራኒዎች ናቸው፡፡
በአለም ያለው ግብዣ ወይም በአጠቃላይ ስጦታ አሰጣጥ መልካም ላደረገልህ ሰው ምላሽ ለመስጠት ነው፡፡
በአለም ግብዣ የምትጋብዘው ሰው ወደፊት ይጠቅመኛል የምትለውን ነው፡፡ እንዲያውም እጅግ ይጠቅመኛል የምትለውንም ሰው ነው መርጠህ የምትጋብዘው፡፡ በአለም ያለው ግብዣ አላማው መጠቀም ነው፡፡
በአለም ያለው ግብዣ አላማው መጠቀም በመሆኑ ምንም ሰማያዊ ሽልማትን አያስገኝም፡፡ ሰው በምድር ለመጠቀም ብሎ ያደረገው ነገር ሁሉ በምድር ይጠቀምበታል እንጂ በሰማይ አይጠቀምበትም፡፡ ሰው በምድር ለመቀበል የሚያደርገው ማንኛውም መስጠት በሰው ልጆች ተመልሶ ይሰጠዋል እንጂ ከእግዚአብሔር የሚሰጠው ምንም ነገር የለም፡፡
ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም። እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። ማቴዎስ 6፡1-2
ሰው ከሰው ለመጠቀም ብሎ የሚያደርገው መጥቀም ምድራዊ ሂሳቡን ይሞላል እንጂ ሰማያዊ ሂሳቡን አይሞላም፡፡
በስሌታችሁ የሚበዛውን ፍሬ እንጂ ስጦታውን ፈላጊ አይደለሁም። ፊልጵስዩስ 4፡17
በክርስትና ከእግዚአብሔር ከፍ ያለ ዋጋ የሚያሰጥህ መስጠት ተመልሶ ሊሰጥህ ለማይችል ሰው መስጠት ነው፡፡ የመስጠት ክብሩ እና ብፅእናው መልሰው ሊሰጡህ ለማይችሉ ሰዎች መስጠት ነው፡፡   
የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃልና።
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #መውደድ #ማድረግ #መስጠት #ምጽዋት #መባረክ #ማካፈል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ሳምራዊ #ሌዋዊ #ካህን #ባልጀራህን #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #ወንጌል

No comments:

Post a Comment