Popular Posts

Tuesday, September 5, 2017

እግዚአብሔር ይፈለጋል!

በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። መዝሙር 105፡3
እግዚአብሔር መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር ባለጠጋ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል፡፡ ሰው ማንንም ባይፈልግ እግዚአብሔርን መፈለግ አለበት፡፡ ሰው ሌላውን ነገር ለመፈለግ ጊዜ ባይሰጥ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ጊዜ መስጠት አለበት፡፡ ሌላ ነገር ሁሉ የሚፈልግ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ሰው ከስሮዋል፡፡
ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች አድርገዋልና እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል፥ የተቀደዱትንም ጕድጓዶች፥ ውኃውን ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጕድጓዶች፥ ለራሳቸው ቆፍረዋል። ኤርሚያስ 2፡13
እውነተኛ መረዳት ሲኖረን እግዚአብሔርን የማንፈልግበት የህይወት ክፍል እንደሌለ እንረዳለን፡፡ እግዚአብሔርን ባወቅነው መጠን ይበልጥ እንፈልገዋለን፡፡ እግዚአብሔርን በተረዳነው መጠን እግዚአብሔር ይበልጥ እንደሚያስፈልገን እንረዳለን፡፡ በእግዚአብሔር ነገር ማደጋችን የሚለካው እግዚአብሔርን ከመቼውም ጊዜ በላይ በመፈለጋችን ነው፡፡ የህይወትን አሰራር በተረዳነው መጠን እግዚአብሔርን ይበልጥ እንፈልገዋለን፡፡
በእግዚአብሔር እውቀት ያለን ብስለት የሚለካው እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በመፈለጋችን ነው፡፡ አዋቂነታችን የሚለካው ከአዋቂዎች ሁሉ በላይ አዋቂ በሆነው በእግዚአብሔር ላይ በመደገፋችን ነው፡፡
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 40፡28
እግዚአብሔር ሙሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያስመካል፡፡ እግዚአብሔር ያኮራል፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ደስ ይበለው፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው እድለኛ ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው የተባረከ ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው ደስ ካላለው ማንም ደስ ሊለው አይችልም፡፡
እግዚአብሔር መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰውን መልካምነት ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልጉትን ይወዳል፡፡ እግዚአብሔር ለሚፈልጉት ብቻ እርሱን በመፈለጋቸው ዋጋ ይከፍላል፡፡
ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራዊያን 11፡4
እግዚአብሔርን ፈልጉት ትፀናላችሁ፡፡ እግዚአብሔርን ስትፈልጉት በእርሱ ታላቅ ሃይል ትገለጣላችሁ፡፡ እግዚአብሔርን በሚፈልጉት ሰዎች ድካም የራሱን ሃይል ይገልጣል፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልጉትን ሰዎች ድካም በብርታቱ ይሸፍናል፡፡  
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። 2ኛ ዜና 16፡9
እግዚአብሄርን ስንፈልገው እንደባጣ ቆየኝ ሳይሆን በአክብሮት በሙሉ ልባችን እንድንፈልገው ይፈልጋል፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፀሎት #ሁሉንቻይ #ጥበኛ #ሁሉበሁሉ #እግዚአብሔር #እግዚአብሔርንመፈለግ #ፀሎት #የዘላለምህይወት #የእግዚአብሔርፈቃድ #የጊዜው #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment