Popular Posts

Saturday, September 16, 2017

የደህንነት ነፃ ስጦታ

ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር ተለያይቶዋል፡፡ ሰው በሃጢያቱ ሙት ሆኖዋል፡፡ ሰው ከዚህ ሞት መዳን አለበት፡፡ ሰው ካልዳነ በስተቀር ለዘላለም ከእግዚአብሄር ይላያያል፡፡
ደህንነት ደሞ ነፃ ስጦታ ነው፡፡ ደህንነት እጅግ ውድ ከመሆኑ የተነሳ ደህንነትን በምንም ነገር ሊገዙት አይችሉም፡፡  
ሰው በሃጢያት የተነሳ በእግዚአብሄር ዘንድ ሙት በመሆኑና ከእግዚአብሔር ጋር ጠላት በመሆኑ በህይወት ዘመኑ ሁሉ መልካምን ስራ ቢሰራ መልካም ስራው ደህንነትን ሊገዛለት አይችልም፡፡
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ኤፌሶን 2፡8-9
መልካ ስራ ደህንትን ቢያስገኝልን ኖሮ ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት አያስፈልገውም ነበር፡፡
መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ቲቶ 2፡14
ሰው በአለም ላይ ያለውን ገንዘብ ሁሉ ቢያፈስ የአንድ ሰውን ደህንነትን ለመግዛት አይበቃም፡፡ ደህንነት እንዳውም በገንዘብ ሊተመን የማይችል እጅግ ውድ ነገር ነው፡፡  
ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? ማርቆስ 8፡36-37
ከጥፋተ መዳን የምንችለው ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለሃጢያታችን ያደረገው መስዋእትነት ለእኔ ነው ብለን በእምነት በመቀበል ብቻ ነው፡፡  
ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።1ኛ ጴጥሮስ 1፡18-19
ሰው ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞት የከፈለለትን የሃጢያት እዳ ክፍያ በእምነት ባይቀበል ለዘላለም ከእግዚአብሄር በመለያየት ይከፍለዋል፡፡ ሰው እግዚአብሄ በክርስቶስ የሰጠውን ነፃ ስጦታ ቸል ቢል ለዘላለም ከእግዚአብሄር በመለያየት ይጠፋል፡፡
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 3፡16
እግዚአብሔር ሆይ ስለላክልኝ ስለደህነነት ቃል አመሰግንሃለሁ፡፡ ልጅህ ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ ሊሰቀል ወደምድር ስለመጣ  ስለሞተልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ኢየሱስ ከሙታን ተለይቶ በሶስተኛው ቀን እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአደፌ እመሰክራለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ልጅህ አድርገህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በጌታ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment