Popular Posts

Friday, September 1, 2017

ሚስቶቻችሁን ውደዱ

ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ። እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል። ኤፌሶን 5፡25-30
የመፅሃፍ ቅዱስ ትእዛዝ ኢየሱስ ተቀብሏችኋል ወዷችኋል ሚስቶቻችሁን ራሩላቸው ተቀበሏቸው ነው፡፡
ኦየሱስ የተቀበለን እንዳለን ነው፡፡ ኢየሱስ እኛን ከመቀበሉ በፊት አልለወጠንም አላሻሸለንም፡፡ ኢየሱስ አኛን የተቀበለን ባለንበት ቦታና ደረጃ ነው፡፡ ኢየሱስ ሲቀበለን እኛን ለመቀበል እና ለመውደድ የሚያበታታ ምንም ነገር አልነበረም፡፡  
ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ኤፌሶን 2፡4-5
ኢየሱስ እኛን የተቀበለን በታላቅነታችን አይደለም፡፡ ኢየሱስ እኘዓን የተቀበለን በዝቅታቸን በማንወደድበት ጊዜ በድካማችን ነው፡፡
ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡26
ክርስቶስ ተረድቶናል፡፡ ክርስቶስ ሊወደን የቻለው ስለተረዳን ነው፡፡ ክርስቶስ ያለንበትን ደረጃ ተረድቶናል ክርስቶስ ራርቶልናል፡፡
ክርስቶስ እንዴት በጥንቃቄ እንደሚይዘን የታውቃል፡፡ ክርስቶስ አንደደረስንበት ደረጃ ይንከባከበናል፡፡ ክርስቶስ በደረስንበርት ደረከጃ ወርዶ የእኛን ቋንቋ ተናግሮ ከእኛ ጋር ኖሮ መስዋእት ሆኖልናል፡፡ ክርስቶስ ሁላችንንም በደረስንበት ደረጃ በፍቅር ይንከባከበናል፡፡
ክርስቶስ ጨካኝ አይደለም፡፡ ክርስቶስ አሳልፎ አይሰጠንም፡፡ ክርስቶስ በድካማችን ዞር አይልም፡፡ ክርስቶስ ርሁርሁ ነው፡፡ ክርስቶስ በድካማችን አይፈርድም፡፡ ክርስቶስ በድካማችንን ይራራልናል፡፡ ክርስቶስ በድካማችን ይሸከመናል፡፡ ክርስቶስ ድካማችንን በብርታቱ ይሸፍናል፡፡
ክርስቶስ ይመግበናል፡፡ ክርስቶስ ያስታጥቀናል፡፡ ክርስቶስ ያበረታታናል፡፡
ክርስቶስ ከእኛ ጋር ራሱ ያስተበናብራል፡፡ ክርስቶስ ለከእኛ ጋር አብሮ ለመጠራት ፈቃደኛ ነው፡፡ ክርስቶስ ከእኛ ጋር መቆጠርን ይፈልጋል፡፡ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ያብራል፡፡ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ይተባበራል፡፡
ስለዚህም ምክንያት፦ ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ፤ ደግሞም፦ እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤ ደግሞም፦ እነሆኝ እኔን እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች ሲል ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም። ዕብራውያን 2፡13
ኢየሱስ ትሁት ነው፡፡ ኢየሱስ ስለእኛ አሳልፎ ሰጠ፡፡ ስለእኛ ራሱን አልሰሰተም፡፡ ስለእኛ ያለውን ሁሉ ሰጠ፡፡ ስለእኛ የሆነውን ሁሉ ሆነ፡፡ ስለእኛ ክብሩን አጣ ተዋረደ፡፡  
በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ፊልጵስዩስ 2፡5-8
 ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #ፍቅር #መውደድ #ይተዋል #ይጣበቃል #አንድስጋ #እውነት #ትህትና #ትንሳኤ #ህይወት #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment