Popular Posts

Wednesday, July 5, 2017

በመንፈስ የመመላለስ ሌላው ትርጉም

በመንፈስ መመላለስ እጅግ ርቆ ያለ ጥቂቶች ብቻ ሊደርሱበትና ሊገቡበት የሚችሉ ልምምድ አይደለም፡፡ በመንፈስ መመላለሰ ማንኛውም በጌታ ኢየሱስ አዳኝነት ያመነ ሰው ሁሉ ሊለማመደው የሚችል የእግዚአብሄርን ፈቃድ የምንፈፅምበት በዚያም እግዚአብሄርን ደስ የምናሰኝበት የእግዚአብሄር አሰራር ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ተመሳሳይ ትርጉሞችን ማየት በመንፈስ መመላለስ ምን ማለት እንደሆነ ተጨማሪ መረዳትን ይሰጠናል፡፡  
በመንፈስ መመላለስ በብርሃን መመላለስ ነው፡፡
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። 1ኛ ዮሐንስ 1፡7
በመንፈስ መመላለስ በእምነት መመላለስ ነው፡፡
ካለእምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻለም፡፡ በእምነት እግዚአብሄርን ደስ መሰኘት ይቻላል፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማለት የሚታየውን አለማየት የማይታየውን ማየት ነው፡፡ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18
እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና፡፡ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡6-7
በመንፈስ መመላለስ በፍቅር መመላለስ ነው፡፡
በፍቅር መመላለስ ማለት እግዚአብሄርንና ሰውን መውደድ ነው፡፡ ለሰው መልካም ማሰብ መልካም መናገርና መልካም ማድረግ ፍቅር ነው፡፡ በፍቅር የሚኖር ህጉን ሁሉ ፈፅሞታል፡፡ ገላትያ 5፡4
እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ። ኤፌሶን 5፡1-2
እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና። ሮሜ 13፡8
በመንፈስ መመላለሰ በጥበበ መመላለስ ነው፡፡
ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። ቆላስይስ 4፡5
እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ኤፌሶን 5፡15
በመንፈስ መመላለሰ በቃሉ መመላለስ ነው፡፡
ቃሉ በሙላት ያለበት ቃሉን የሚያሰላስል ከቃሉ ውጭ የማያስብ ሰው በመንፈስ ይመላለሳል፡፡
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ዮሃንስ 15፡7
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ሮሜ 8፡5
በመንፈስ መመላለስ በሰማያዊ ሃሳብ መመላለስ
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2
በመንፈስ መመላለሰ በእውነት መመላለስ
ወንድሞች መጥተው አንተ በእውነት እንደምትሄድ ስለ እውነትህ ሲመሰክሩ እጅግ ደስ ብሎኛልና። ልጆቼ በእውነት እንዲሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለኝም። 3 ዮሐንስ 1፡4
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #በመንፈስመመላለሰ #ቃሉንማሰላሰል #መንፈስበእኛ #ህግንመፈፀም #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሔርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ፍቅር #እውነት #እምነት #ብርሃን #ሰማይ

No comments:

Post a Comment