Popular Posts

Sunday, June 18, 2017

የአባት ቁልፍ ሃላፊነቶች


  • አባት ምሪትን የሚያቀርብ ነው
አባት ስለቤተሰቡ ራእይ ያለው ነው፡፡ አባት ቤተሰቡ ወዴት መሄድ እንዳለበት እይታው አለው፡፡ አባት ለቤተሰቡ ራእይን ይሰጣል፡፡ አባት ለቤተሰቡ ግብንና አቅጣጫን ይሰጣል፡፡
  • አባት አቅርቦትን የሚያቀርበ ነው፡፡

አባት ለቤተሰቡ ያዘጋጃል፡፡ አባት ለቤተሰቡ ለማቅረብ ጠንክሮ ይሰራል፡፡ አባት ቤተሰቡ እንዳይጎድልብት ይተጋል፡፡  
  • አባት ለቤተሰቡ ደረጃን የሚሰጥ ነው፡፡

አባት ለቤተሰቡ የኑሮ ደረጃን ይሰጣል ፡፡ አባት የቤተሰቡን የመኖር ትርጉም ይወስናል፡፡ አባት የቤተሰቡ ዋጋ አሰጣጥ ይወስናል፡፡ አባት ያከበረው በቤተሰቡ ውስጥ ይከበራል፡፡  አበናት የናቀው በቤተሰቡ ውስጥ ይናወቃል፡፡ አባት ለሰማያዊ ነገር ከለእግዚአብሄርን መንግስት ዋጋ የሚሰጥ ከሆነ ቤተሰቡ ይከተላል፡፡ አባት እግዚአብሄርን የሚፈራ ከሆነ ልጆች እግዚአብሄርን እየፈሩ እንዲያድጉ ያለመቻችላቸዋል፡፡ አባት የምድራዊውን ነገር የሚንቅ ከሆነ ልጆች በአባታቸው ጥላ የምድራዊውን ነገር ለመናቅ ጥላ ይሆንላቸዋል ያመቻችላቸዋል፡፡
  • አባት ለቤተሰቡ ጥላን ይሰጣል፡፡

አባት ተጋፋጭ ነው፡ አሽቸጋሪ ነገር ሲመጣ አባት ቤተሰቡን አያጋፍጥም ራሱ ይጋፈጣል፡፡ አባት ቤተሰቡን ከልሎ ይዋጋል፡፡ አባት ጥላ ይሆናል፡፡ አባት ቤተሰቡ ላይ እንዳይደርስ አስከፊውን ነገር ራሱ ይቀበላል፡፡ አባት ስሜቱን ዋጥ ያደርጋል፡፡ ቤተሰብ በአባት ጥላ ያድጋል ይገለብታል፡፡ በተራው አባት ለመሆን ይኮተኮታል፡፡   
  • አባት ስለቤተሰቡ ሃላፊነትን ይወስዳል፡፡

አባት የቤተሰቡ አባት ባጠፋው ይጠየቃል፡፡ አባት ቤተሰቡን ይሸከማል፡፡ አባት ስለቤተሰቡ ሃላፊነት ይወስዳል፡፡ አባት የቤተሰቡን አባል ለትችት አሳልፎ አይሰጥም፡፡ አባት በቤተሰቡ ያምናል፡፡ ሌላ ማንም በቤተሰቡ ባያምን አባት ስለቤተሰቡ መጀመሪያ የሚያምን ነው፡፡ አባት ቤተሰቡን ይወዳል ፡፡ አባት የቤተሰቡ የመጀመሪያ አድናቂ ነው፡፡
  • አባት ቤተሰቡን ያበረታታል፡፡

አባት ቤተሰቡን ያበረታታል፡፡ በአስቸጋሪ ጊዜ ስለቤተሰቡ የተሻለ ነገር ያምናል፡፡ አባት ተስፋ ከቆረጠ ቤተሰብ ለመነሳት ይቸግረዋል፡፡ አባት ከደፈረ ቤተሰብ ለመነሳት አቅም ያገኛል፡፡
መልካም የአባቶች ቀን!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ወላጅ #ፍቅር #አባት #እርማት #ጥንካሬ #ራእይ #ደረጃመስጠት #ጥላ #ማበረታታት #አባትነት #ተግሳፅ  #መሪ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment