Popular Posts

Monday, June 5, 2017

የብልፅግና ወንጌል

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር አምሳል ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው በሙላት ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው የእግዚአብሄር የቤተሰብ አባል እንዲሆን ነው፡፡
ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄ ክብር ወደቀ፡፡ የእግዚአብሄር ልጅ እንድንሆን በክርስቶስ የሃጢያታችን እዳ ሁሉ በክርስቶስ ተከፈለ፡፡
ወንጌል የምስራች ቃል ነው፡፡ ወንጌል ስለ መዳን መንገድ አብሳሪ ነው፡፡ ወንጌል የሙላት መልእክት ነው፡፡ ወንጌል የእግዚአብሄር የማዳን ሃይል ለሰው የተገለጠበት መልእክት ነው፡፡ ወንጌል የብልፅግና መልእክት ነው፡፡
ወንጌል በክርስቶስ ስለተዘጋጀልን የሙላት ህይወት ይናገራል፡፡  
እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሃንስ 10፡10
ወንጌል ስለነፃ ስጦታ ይናገራል፡፡
ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። ዮሃንስ 1፡14
ወንጌል ስለ አዳነን የእግዚአብሄር ፀጋ ባለ ጠግነት ይናገራል፡፡
በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ። በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን። ኤፌሶን ሰዎች 1፡6-8
ወንጌል ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ስለ ሆነው ስለ እግዚአብሄር ይናገራል፡፡
መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና። በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ሮሜ 10፡11-12
ወንጌል በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነው ስለአባታችን ስለ እግዚአብሄር ይናገራል፡፡
ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ኤፌሶን ሰዎች 2፡4-5
ወንጌል ስንደክም እንኳን በሃይሉ ድካማችንን ስለሚሞላው ስለ ጌታ ይናገራል፡፡
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡10
ወንጌል ሃጢያት ሲበዛ ከመጠን ይልቅ ስለሚበልጥ ፀጋ ያውጃል
እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ። ሮሜ 5፡20-21
ወንጌል ሃይል በክርስቶስ ሁሉን ስለሚያስችል እግዚአብሄር ይናገራል
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡13
ወንጌል እንደ ባለጠግነቱ መጠን የሚያስፈልገንን ሁሉ ስለሚሞላብን እግዚአብሄር ይናገራል
አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19
ወንጌል እረኛችን ስለሆነና የሚያሳጣን ስለሌለ ጌታ ይናገራል
በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል። ዮሃንስ 10፡9
ወንጌል በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ስለባረከን ጌታ ይናገራል
በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። ኤፌሶን 1፡3
ወንጌል የሚያስፈልገንን ሁሉ ሊሞላብን ስለሚችለው ስለእግዚአብሄር ይናገራል
እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል። 2ኛ  ቆሮንቶስ 9፡8-9
ወንጌል ሁሉ የእናንተ ነው ስላለው ጌታችን ይናገራል
ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤ ጳውሎስ ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሕይወትም ቢሆን ሞትም ቢሆን ያለውም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን፥ ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡21-23
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment