Popular Posts

Tuesday, April 4, 2017

ለፍቅር የፈጠረው ሰው

ሰው ለመውደድ እና ለመወደድ ታልሞና ታቅዶ ነው የተፈጠረው፡፡ ሰው ከመውደድና ከመውደድ ውጭ ሲወጣ ህይወቱ ይዛባል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ለመውደድ ሰውን ለመውደድ ተፈጥሯል፡፡
ፍቅር ስለሌላው መልካም ማሰብ ፣ መልካም ማድረግና መልካም መናገር ነው፡፡ ፍቅር በመረዳት ከሌላው ጋር ራስን ማስተባበር ነው፡፡  
ሰው ከሁሉም በላይ በእግዚአብሄር ተወዷል፡፡ ሰው በእግዚአብሄር እንደ ተወደደ ካላወቀ ህይወቱ በምንም ነገር ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ነው ምንም ነገር ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ እያለ ሃዋሪያው የሚያስተምረው፡፡ የሰው እውነተኛ ጥቅም በፍቅር መኖር ነው፡፡ የሰው ልጅ የመኖር ትርፉ በፍቅር መመላለስ ነው፡፡
በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡2-3
ሰው ምንም ነገር ቢኖረው ፍቅር ከሌለው ምንም አይጠቅመውም፡፡ የሰው ክብሩና ውበቱ በፍቅር መኖር ነው፡፡ የሰው ዋጋውና ክብደቱ በፍቅር መኖሩ ነው፡፡ ሰው ፍቅር ከሌለው ምንም አይጠቅመውምም ምንም አይጠቀምም፡፡   
ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 1 ቆሮንቶስ 13፡3
ሰው በተፈጠረበት ንድፍ በፍቅር ሲኖር ይቀለዋል፡፡ ሰው ግን በጥላቻ ሲኖር ባልተሰራበት ዲዛይን ስለሚኖር ሁሉ ነገር ይወሳሰብበታል፡፡ ሰው በፍቅር ሲኖር በግልፅና በብርሃን ይኖራል፡፡ ጥላቻን በድብቅና በጨለማ ስለሚያደርገው ህይወቱን ያወሳስብበታል፡፡ ሰው በፍቅር ሲኖር ብቻ በነፃነት ይኖራል፡፡
ሰው ለፍቅርና ለመልካም ስራ ተፈጥሯል፡፡
ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ ዕብራዊያን 10፡24

#ኢየሱስ #ጌታ #ፍቅር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ዲዛይን #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ንድፍ #መንፈስቅዱስ #እቅድ #ልብ #መውደድ #የህግፍፃሜ

No comments:

Post a Comment