Popular Posts

Sunday, April 2, 2017

በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ

ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡24
ለሰው ልጆች የእግዚአብሄር ፈቃድ ጤንነት ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ጠንካራና ጤነኛ አድርጎ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረው ከአንድም በሽታ ጋር አልፈጠረውም፡፡ በእግዚአብሄር የሰው ፍጥረት ዲዛይን ውስጥ በሽታ የሚባል ተሰምቶ አይታወቅም፡፡ እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥረው አንድም በሽታ በምድር ላይ አለመኖሩ የሚያሳየው እግዚአብሄር ለሰው ልጅ በፍፁም የበሽታ እቅድ እንዳልነበረው ነው፡፡
ሰው በሃጢያት በወደቀ ጊዜ ግን በሽታ ወደምድር ገባ፡፡ ከዚያም በኋላ ቢሆን እግዚአብሄ በሰዎች ስቃይ ተደስቶ አያውቅም፡፡ የእግዚአብሄር ፈቃድ የሰዎች መፈወስ ነው፡፡
ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ለነፍሳቸው መፍትሄ ብቻ አልነበረም ፡፡ ኢየሱስ ለስጋቸው ፈውስ መፍትሄም ይዞ መጥቷል፡፡ ኢየሱስ ለነፍሳችን ፈውስ ሲሞት ለስጋችን ፈውስ ተገርፏል፡፡
እኛ ሃጢያትን እነዳንሸከም ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለነፍሳችን ሞተ፡፡ እኛ በሽታን እንዳንሸከም ኢየሱስ በመስቀል ተገረፈ፡፡ ኢየሱስ ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞ ነበር፡፡  
በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። ኢሳይያስ 53፡4
ስለዚህ ነው ኢየሱስ በምድር ላይ በየስፍራው እየዞረ የታመሙትን ሁሉ በትጋት ይፈውስ የነበረው፡፡  
በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ፦ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ። ማቴዎስ 8፡16-17
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ፈውስ #እምነት #ቁስል #ህመም #ደዌ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #በመገረፉ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment