Popular Posts

Saturday, April 15, 2017

ተነሥቷል

አዝ፦ ተነሥቷል (2x) የመቃብር ደጃፍ ተከፍቷል
ድንጋዩ በሩቅ ተንከባሏል
ከፈኑ ብቻ ነው አስክሬኑ የታል?
በእውነትም ኢየሱስ ድል ነሥቷል (2x)

ኢየሱስ ማሸነፉን ይስማ ኢየሩሳሌም
ይውጣ ምሥራቹ ከዓለም እስከዓለም
ይስማኝ ጠላትም መርዶውን አልቅሶ
ጌታ እንደው ተነስቷል አይሞት ተመልሶ

አዝ፦ ተነሥቷል (2x) የመቃብር ደጃፍ ተከፍቷል
ድንጋዩ በሩቅ ተንከባሏል
ከፈኑ ብቻ ነው አስክሬኑ የታል?
በእውነትም ኢየሱስ ድል ነሥቷል

ይወገድ ድንጋዩ ጠባቂውም ይምጣ
ኢየሱስን ካቃተው ጌታ መውጫ ካጣ
የትኛው ጠባቂ ነው የከለከለው
ጌታ መቃብሩን ሲፈነቃቅለው

አዝ፦ ተነሥቷል (2x) የመቃብር ደጃፍ ተከፍቷል
ድንጋዩ በሩቅ ተንከባሏል
ከፈኑ ብቻ ነው አስክሬኑ የታል?
በዕውነትም ኢየሱስ ድል ነሥስቷል

ይነገር ለዓለም ምስራች ይሰማ
ሞትን አሸንፏል ጀግናው ኢየሱስማ
ይህ ሐሰት አይደለም ዘለዓለም እውነት ነው
ይታይ የጌታችን መቃብር ባዶ ነው

አዝ፦ ተነሥቷል (2x) የመቃብር ደጃፍ ተከፍቷል
ድንጋዩ በሩቅ ተንከባሏል
ከፈኑ ብቻ ነው አስክሬኑ የታል?
በእውነትም ኢየሱስ ድል ነሥቷል

ይሄ ነው እንግዲህ የጐልጐታው ሚስጥር
ወንጌላችን ኢየሱስ ከሙታንም በኩር
ሙትን አናመልክም መቃብር የዋጠ
ያሸነፈን እንጂ ሞትን ድል የነሳ

አዝ፦ ተነሥቷል (2x) የመቃብር ደጃፍ ተከፍቷል
ድንጋዩ በሩቅ ተንከባሏል
ከፈኑ ብቻ ነው አስክሬኑ የታል?
በእውነትም ኢየሱስ ድል ነሥቷል


መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

No comments:

Post a Comment