Popular Posts

Thursday, March 9, 2017

ነፍሱን የሚያጠፋ

ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል። ማርቆስ 8፡34-35  
ኢየሱስ ስለሃጢያታችን ነፍሱን ነው የከፈለው፡፡ ኢየሱስም ከእኛ ሙሉ መሰጠትን ነው የሚጠይቀው፡፡ ስለእኛ ሞተው ሙሉ ለሙሉ ለእርሱ እንድንኖርለት ይፈልጋል፡፡ ከነፍሳችን ፍላጎት በላይ የእርሱን ፍላጎት እንድናስቀድም ጌታ ይፈልጋል፡፡ ጌታን ለመስማትና ለመታዘዝ ነፍሳችንን አለመስማትና አለመታዘዝ ይጠብቅብናል፡፡ ለጌታ እሺ ለማለት ነፍሳችንን መካድ ል፡፡   
በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡15
ኢየሱስ ለጎዶሎ መሰጠት አልጠራንም፡፡ የክርስትና ህይወት ሃላፊነቱን ተሸክሞ የማይከተል የኢየሱስ ደቀመዝሙት ሊሆን አይገባውም፡፡
ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። ሉቃስ 14፡27
እውነተኛ ህይወት የሚገኘው ጌታን ሙሉ ለሙሉ በመከተል ነው፡፡ ሙሉ ፍሬያማነትም የሚመጣው ጌታን ካለመቆጠብ በመከተል ነው፡፡
በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል። ዮሃንስ 15፡7-8
ሰው እውነተኛ ነፃነት ውስጥ የሚገባውና ነፃነትን የሚለማመደው በደቀመዝሙርነትና ሙሉ ለሙሉ ጌታነ በመከተል ነው፡፡
ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። ዮሐንስ 8፡31-32
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #መከተል #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ደቀመዝሙር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ነፍስንመካድ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment