Popular Posts

Friday, March 24, 2017

የማሪያም ፀሎት

በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ልቤን ከሚነኩኝ ፀሎቶችና ንግግሮች መካከል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ማሪያም የፀለየችው አንዱ ነው፡፡
ማርያምም እንዲህ አለች፦ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው። ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል። በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤ የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል። ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል። ሉቃስ 1፡46-55
ማሪያም በእግዚአብሄር አሰራር ደስተኛ ነበረች፡፡ እግዚአብሄር ለዚህ ታላቅ ስራ ስለተጠቀመባት ታመሰግናለች፡፡  
#47 ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
ንግግርዋ በእግዚአብሄር ላይ ባለ እምነት የተደረገ ነበር፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል የምታከብር ብፅዕት ነበረች፡፡
#38 ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ስለሚሏት እንኳን እግዚአብሄርን ታመሰግናለች፡፡   
#48-49 . . . እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።
ማሪያም ትሁት ነበረች፡፡ የእግዚአብሄር አገልጋይ እንደሆነች ታውቃለች፡፡   
#48 የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና።
ማሪያም ለእግዚአብሄር ክብር የምትሰጥ ነበረች፡፡
#49 ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ድንግል #ፀሎት #ልመና #ብፅዕት #ማሪያም #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #ምስጋና

No comments:

Post a Comment