Popular Posts

Friday, January 20, 2017

አክሊል ተዘጋጅቷል

የኢየሱስን አዳኝነት አምነን የተቀበልን ሁላችን ወደጌታ ስንሄድ ወይም ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ በእግዚአብሄር የፍርድ ፊት ቀርበን ሽልማታችንን እንቀበላለን፡፡
ነገር ግን ሁሉም ሁሉን አይነት ሽልማት አይቀበልም፡፡ እውነት ነው ደህንነት በነኛ ነው፡፡ ደሀንነት ኢየሱስ በሰራው መስዋእትነበት በማመን ብቻ የምንቀበለው ስለሆነ ለሁሉም ነው፡፡ ሰው ለመዳን ኢየሱስ በሰራው የመስቀል ስራ ከማመን ውጭ ምንም አይነት ስራ መስራት የለበትም፡፡
በእሳት ስለሚገለጥ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል። ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡13-15
ነገር ግን ሽልማቱ ለሁሉም አይደለም፡፡ እንደሚገባ ለሚታገሉ ፣ የመታገያውን ህግ ለሚጠብቁ ፣ ረሳቸውን ለሚገዙ ፣ ምንም ይሁን ምን በፍቅር ለመኖር ለሚወስኑ ፣ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ ዋጋ ለሚከፍሉ ፣ ራሳቸውን ለሚክዱ ፣ ባላቸው ነገር ሁሉ ቤተክርስትያንን ለሚያገለግሉ ፣ ለእግዚአብሄር መንግስት መስፋፋት ጊዜያቸውን ፣ ጉልበታቸውን ፣ ገንዘባቸውን ፣ እውቀታቸው ሳይሰስቱ ለሚሰጡ ሰዎች ብቻ ነው፡፡   
ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም። 2 ጢሞቴዎስ 25
የሚያሳዝነው ግን እንዳንድ ሰዎች ያደረጉትን መልካም ነገር ሁሉ ዋጋ በምድር ላይ ይቀበሉታል፡፡
ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና። ሉቃስ 6፡22-24
በምድር ስንኖር መከራ አለ፡፡ የጠላት የዲያቢሎስ መንግስት ይሰራል፡፡ በምድር ላይ ለእግዚአብሄር ስንኖር ፣ የእግዚአብሄርን መንግስት ስናስፋፋና እግዚአብሄር በህይወታቸን ያስቀመጠውን የመንግስቱን አላማ ስናስፈፅም ሊያስቆመን መከራን ያመጣብናል፡፡ ነገር ግን የታመንን ከሆንን የህይወት አክሊል ለእኛ ይሆናል፡፡  
ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ። ራእይ 2፥10
በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና። ያዕቆብ 112
በምድር እንኳን ሰው ለምድራዊ ሽልማት ተግቶ ይሰራል፡፡ የምድራዊውን ለመሸለም ሰው ራሱን ይገዛል፡፡ የሚያምረውን አይበላም ፣ የሚያምረውን አይለብስም የሚያምረውንም አይጠጣም፡፡ ለምድራዊ ሽልማት ሰው እንደዚህ ራሱን ካስገዛ እኛማ ለዘላለማዊው ለማይጠፋው ሽልማት እንዴት ሌት ተቀን አንሰራም፡፡
የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን። 1 ቆሮንቶስ 925
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #አክሊል #ሽልማት #ትንሳኤ #ሰማይ #የማይጠፋአከሊል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ


No comments:

Post a Comment