Popular Posts

Sunday, November 6, 2016

መንፈስ የምንሞላባቸው መንገዶች

መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤ ኤፌሶን 5፡18
የእግዚአብሄርን ነገር በመንፈስ ነው የሚሰራው፡፡ የተለያዩ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንችላለን ካለ መንፈስ ሙላትና እርዳታ ግን የእግዚአብሄርን ስራ በብቃት መፈፀም አንችልም፡፡
ስለዚህ ነው መንፈስ ይሙላባችሁ ብሎ መፅሃፍ ቅዱስ የሚመክረው፡፡ አንድ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ከተሞላንና በልሳን ወይም በአዲስ ቋንቋ ከተናገርን በኋላ ደግመን ደጋግመን በመንፈስ መሞላት ይገባናል፡፡ በመንፈስ የምንሞላባቸው አራቱ መንገዶች
1. ፀሎት
ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ። ሐዋርያት 4፡31
2. ቃልን ማንበብ
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው። ዮሐንስ 6፡63 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16-17
3. አምልኮ
መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤ ኤፌሶን 4፡18-19
4. በመከራ መፅናት
ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 4፡14
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #ሙላት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠመቅ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment