Popular Posts

Thursday, November 10, 2016

ፍፁም ፍቅር

ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። 1ኛ ዮሐንስ 4፡18
ፍርሃት የሰዎችን ጉልበት የሚበላ ከፍፃሜያቸው ሊያስቆማቸው የሚመጣ ጠላት ነው፡፡
ፍቅር ደግሞ ንፁህ ነው፡፡
ፍቅር ስለሌለው መልካም ማሰብ ፣ ስለሌላው መልካም መናገርና ስለሌላው መልካም ማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ ነው በፍቅርና በሌሎች የመንፈስ ፍሬዎች ላይ የሚሰራ ህግ እንደሌለ መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ገላትያ 5፡22-23
ሰው በምንም ነገር ቢከሰስ ለሰው መልካም አሰብክ ተብሎ አይከሰስም፡፡ ሰው ምንም ነገር ቢከለከል ለሰው መልካም መናገር አይከለከልም፡፡ ሰው በምንም ነገር ቢፈረድበት ለሰው መልካም አደረክ ተብሎ አይፈረድበትም፡፡
ፍቅር ደግሞ ከሁሉ ይበልጣል፡፡
የፍቅር ህይወት ከፍ ያለ ህይወት ነው፡፡ ንስርን የመሬት ሁኔታ እንደማይዘውና ንፋሱ በበረታ ቁጥር ከፍ እንዲል እንደሚያደርገው ሁሉ በፍቅር የሚኖር ሰው ከነገሮች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ህይወት ነው የሚኖረው፡፡
እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡13
ፍርሃት ብዙዎችን ከመንገዳቸው ያሰናከለ ፈታኝ ጠላት ነው፡፡ ፍቅር ደግሞ ከፍርሃት ሁሉ በላይ ነው፡፡ ፍርሃት በህግና በደንብ ላለመኖር ከመፈለግ ይመጣል፡፡ ፍቅር በህጉ መሰረት ቅጣት ላይ ላለመውደቅ የሚሰማን ስሜት ነው፡፡
ፍቅር ግን ከህግ በላይ ስለሚኖር በፍቅር ፍርሃት የለም፡፡ ፍቅር የሚቀጥለውን ምዕራፍ የሚሄድ ስለሆነ ፍቅር ከፍርሃት በላይ ያደርገናል፡፡ ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥለዋል፡፡
ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። 1ኛ ዮሐንስ 4፡18
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ፍቅር #መንፈስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ፍርሃት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ትዕግስት #መንፈስቅዱስ #ምስክር #ልብ #መሪ

No comments:

Post a Comment