Popular Posts

Tuesday, October 11, 2016

እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 9፡23-24

ሰው  ባለው ነገር ለመመካት ሁልጊዜ ይፈተናል፡፡ ነገር ግን ያለን ማንኛውም ነገር ቋሚ አይደለም፡፡ ያለን ማንኛውም ነገር ሊመኩበት የሚያስችል በቂ አይደለም፡፡ ያለን ማንኛውም ነገር ጎዶሎና ደካማ ነው፡፡

ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሄር ላይ እንዲደገፍ ነው፡፡ ሰው ግን ባለው በማንኛውም ነገር ሲመካ ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነቱ ይበላሻል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ላይ አይኑን ሲያነሳ ሁሉ ነገሩ ይዘባረቃል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ውጭ ለራሱ መጠጊያ ሲፈልግ መውደቅ ይጀምራል፡፡

ሰው ሁልጊዜ በእግዚአብሄር ላይ ብቻ መመካትን መማር አለበት፡፡ ሊያስመኩ የሚችሉትን ነገሮቻችንን ወደጎን በማድረግ በእግዚአብሄር ሃይል ላይ መደገፍ አለብን፡፡ እኔ አለሁልህ የሚሉትን ነገሮች መርሳት አለብን፡፡ ከእግዚአብሄር በቀር ምንም ነገራችን ላይ ልባችንን መጣል የለብንም፡፡   

ሰው ሁልጊዜ በእግዚአብሄር ላይ ብቻ ለመመካት ራሱን ማስለመድ አለበት፡፡ ሰው ሁልጊዜ ሌሎች በሚያስመኩ ነገሮች ላይ ላለመመካት እምቢ ማለት አለበት፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ውጭ በሌላ በምንም ነገር እንዳይመካ መጠንቀቅ አለበት፡፡

እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 24

እምነት ማለት በእግዚአብሄር ላይ መታመንና መደገፍ ነው፡፡ እምነት ማለት ቅን መሆን ነው፡፡ እምነት እግዚአብሄርን በቃሉ መያዝ ነው፡፡ እምነት እግዚአብሄርን ያለውን በቅንነት መቀበል ነው፡፡ እምነት አለመኩራትና ትህትና ነው፡፡ እምነት ከእግዚአብሄር ውጭ በምንም ነገር ላይ አለመደገፍ ነው፡፡ ፃዲቅ ግን በትህትና በህይወት ይኖራል፡፡

ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ



#ኢየሱስ #ጌታ #መመካት #መታመን #እምነት #ቅንነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment