Popular Posts

Friday, September 30, 2016

አስተማሪ መንፈስ ቅዱስ

ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ያስተምራቸው ይመራቸው ነበር ፡፡ ኢየሱስ የመሄጃው ጊዜ ሲደርስ ደቀመዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፡፡ ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፡፡

ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ። ዮሐንስ 14፡15-16

ኢየሱስ ሲመራቸውና ሲያፅናናቸው ለነበሩት ደቀመዛሙርት እኔ አብን እለምናለሁ ከእናንተ ጋር የሚኖር ሌላ አፅናኝ ይሰጣችኋል አላቸው፡፡

ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ ዮሐንስ 14፡15

የተሰጠን መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ጊዜ በእኛ ላይ የሚያርፍ ሳይሆን በእኛ ውስጥ በመኖር የሚመራንና የሚያፅናናን የሚረዳን የሚመራን የሚደግፈን የሚያስተምረን ጠበቃ የሚቆምልን መንፈስ ነው፡፡

እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።ዮሐንስ 14፡17

ይህን መንፈስ አለም ስለማያየው አይቀበለውም እኛ ግን በውስጣችን ስለሞኖርና ስለሚመራን ስለሚናገረን ስለሚያስተምረን እናውቀዋለን፡፡

አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። ዮሐንስ 14፡16

እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡20፣27

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes


#ኢየሱስ #መንፈስቅዱስ #አፅናኝ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ቅባት #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መውደድ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment