Popular Posts

Thursday, September 1, 2016

ራዕይ ግዴታ ነው!



ሰው በህይወት እንዲከናወንለት የሚያስፈልገውን ነገር ማድረግ አለበት እንጂ ሰው በድንገት እንደ እድል አይከናወንለትም፡፡
በህይወይት ለመከናወን ራዕይ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ ራዕይ የሌለው ሰው የትም አይደርስም፡፡ ሰው ህይወቱን በሚገባ ተጠቅሞ ፍሬያማ እንዲሆን ራዕይን መከተል ወሳኝ ነው፡፡
ራዕይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተመሰገነ ነው። ምሳሌ 29፡18
ሰው ራዕይ አለው ወይም ባለራዕይ ነው የሚባለው ለህይወቱ የእግዚአብሄርን ሃሳብ ወይም አጀንዳ ሲያውቅና ሲከተል ነው፡፡
  • ራዕይ ምኞት አይደለም፡፡
በህይወታችን የምንመኛቸው ውይ ይህ ቢሆንልኝ የምንላቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ መልካም ናቸው አንዳንዶቹ ግን መልካም ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ራዕይ ግን የሰው ምኞች በራሱ ሊደርስበት የሚፈልገው ነገር አይደለም፡፡ራዕይ የሰው ምርጫና ፍላጎት አይደለም፡፡
  • ራዕይ እድል አይደለም፡፡
ራዕይ በሃገሪቱ ላይ ያለውን የስራ እድል ወይም በአካባቢው ያለውን ክፍተት በመመልከት የሚመርጡት የስራ እድል አይደለም፡፡ ራዕይ በመመልከት የምንከተለው ነገር አይደለም፡፡ ራዕይ ምድራዊ እውቀታችንን አሰባስበን የምንገነባው የፕሮጀክት እቅድ አይደለም፡፡ ይህ ራዕይ ሳይሆን ይህ ምድራዊ እውቀት ነው፡፡
  • ራዕይ ማየት ነው
ራዕይ የእግዚአብሄርን የተለየ አጀንዳ ማየት ነው፡፡ ራዕይ እግዚአብሄር በልቡና በነፍሱ እንዳለ ማድረግ ነው፡፡

የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፤ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ እኔ በቀባሁት ሰው ፊት ይሄዳል። 1ኛ ሳሙኤል 2፡35

እነርሱም ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ። በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ ብሎት ነበርና። ዕብራዊያን 8፡5

ራዕይ እግዚአብሄር ስለህይወታችን ያየውን አይቶ መከተል ነው፡፡ በራዕይ ስንመራ እግዚአብሄር አብሮን ይቆማል፡፡ የጉዞዋችን ሁሉ ወጪው በእርሱ ነው፡፡ ስራውን ለመፈፀም የሚያስፈልገውን አቅራቦት ሁሉ ይሰጠናል ያበረታናል እንዲሁም በየጊዜው ይመራናል፡፡

በዚህም እግዚአብሄር በምድር ላይ ያዘጋጀልንን ስራ ሰርተን በምድር እናከብረዋለን፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ


No comments:

Post a Comment