Popular Posts

Saturday, September 3, 2016

በፖለቲካ ውጥረት ወቅት ክርስቲያን ማድረግ የሌለበት 5 ነገሮች

ፖለቲካ ውጥረት ሲነግስ ክርስቲያኑ ምን ማድርግ እንዳለበት የሚመክረው ብቸኛ መካሪ የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ሚዛናዊነቱን የጠበቀ ድርጊቶችን ብቻ በማድረግ በዚህ ጊዜ ለሌሎች መልካም ምሳሌ ለመሆን ይህን እድል መጠቀም ይኖርብናል፡፡
  1. ጥበብን አለመጣል
እንደ ክርስቲያን እያንዳንዱ ነገሮቻችን በሌሎች ሰዎች እንደሚታይና በዚህ ጊዜ ለሌሎች በጎ ወይም ክፉ ምሳሌ እንደምንሆን በማወቅ የምናደርገውን ነገር ሁሉ በእርጋታና በጥበብ ማድረግ፡፡ ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን። ቆላስይስ 4፡5-6
2. ራስን ከጥላቻ መጠበቅ፡፡
በጥላቻ መስፋፋት የሚጠቀመው ሰይጣን ብቻ መሆኑን አውቆ ከጥላቻ ራስን መጠበቅ፡፡ ለዚህም ጥላቻን የሚያሰራጩ ንግግሮችን በማስተዋል መስማት፡፡ ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። ኤፌሶን 4፡26-27
3. ሰለአገር መፀለይን አለመተው
በዚህ ሁኔታ ሁሉ እግዚአብሄር ጣልቃ እንዲገባና ከሁሉም በላይ የእግዚአብሄር ፈቃድ በምድሪቱ ላይ እንዲፈፀም መፀለይ፡፡ እንዲሁም ሰይጣን ምንም እድል ፈንታ እንዳይኖረው አጥብቆ መፀለይ፡፡
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1-4
4. በፖለቲካ ከወንድም አለመለየት
ክርስቲያን ስለሆነ ብቻ ሌላው ተመሳሳይ የፖለቲካ አቋም ይኖረዋል ብሎ አለመጠበቅ፡፡ ለተለዩ የፖለቲካ አቋሞች ልብን ማስፋት በዚህም የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ መትጋት በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። ኤፌሶን 4፡2-3
5. ክርስትናን ማስቀደም
እንደ ህዝብ በፖለቲካ ሙሉ ተሳትፎ ማድረግ ቢጠበቅብንም የክርስትናን ባህሪ እስከመጣል ድረስ በፖለቲካ አለመወሰድ ይጠይቃል፡፡ ለምንም የፖለቲካ አስተሳሰብ የማያልፈውን የእግዚአብሄርን መንግስት ስራ አለመተው፡፡ የዘላለሙን የጌታን አገልግሎት በፖለቲካ አቋም አለመለወጥ፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakum...

No comments:

Post a Comment