Popular Posts

Saturday, August 27, 2016

የስደት ብፅዕና

ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ማቴዎስ 5፡10
አለም በክፉ ተይዞአል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ሲያመልክና ሲከተል ከብዙ ሰዎች መካከል ተለይቶ ይወጣል፡፡ በክርስትና ለጌታ ብለን የምንተወውና መስዋዕት የምናደርገው ብዙ ነገር አለ፡፡ ሰዎች አለማዊ የሚሆኑት እውነት መስሎዋቸው ግን ተታለው ነው፡፡ ሰው ዘላለማዊ እንደሆነ የእግዚአብሄ ፍርድ እንደሚመጣ ዘንግተው ወይም ጨልሞባቸው ነው፡፡
ሰው ግን ከመካከላቸው ወጥቶ ጌታን መከተል ሲጀምር በአስተሳሰቡ ሲለይ የእግዚአብሄርን ቃል ሲረዳ ህይወቱን በእግዚአብሄር ቃል ሲመራ የቀሩት ሰዎች ደስተኛ አይሆኑም፡፡ የክርስቲያን መለየት እረፍት ይነሳቸዋል፡፡ በሃይማኖት አሳበውም ይሁን በሌላ ይቃወማሉ፡፡
የቆሸሸ ልብስ የለበሱ ሰዎች በመካከላቸው ንፁህ ልብስ የለበሰ ሰው ሲገኝ መቆሸሻቸውን እንደሚያስታውሳቸውና ምቾት እንደማይሰጣቸው ሁሉ ክርስቲያኑ እግዚአብሄርን ሲፈራ እግዚአብሄርን የማይፈሩትን ያስፈራራቸዋል፡፡ ምንም ቃል ሳይጠቀም
በህይወቱ ብቻ እኔ ወደ መንግስተሰማያት እየሄድኩ ነው እናንተስ ብሎ ይጠይቃቸዋል፡፡ እነርሱ ግን ያ መተማመን ስለሌላቸው ይቃወማሉ፡፡ ክርስቲያኑ ህይወቱን በንፅህና ሲጠብቅ እንደፈለጉ የሚኖሩትን በኑሮው ብቻ ይኮንናቸዋል፡፡
ሰይጣንም ከመንግስቱ ወጥተን እየሱስን ስንመርጥ እርሱን እንደተውነውና እንደካድነው ስለሚያውቅ ህይወታችንን ሊያከብድ ሰዎችን ያስነሳብናል፡፡
በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ። 2ኛ ጢሞቲዮስ 3፡12
ስለዚህ እግዚአብሄርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ስለፅድቅ ነገሮችን ያጣሉ፡፡ ስለ ፅድቅ ከበሬታቸውን ያጣሉ፡፡ ስለፅድቅ ስማቸውን ያጣሉ፡፡ ስለፅድቅ ምቾታቸውን ይተዋሉ፡፡ ስለፅድቅ ይታሰራሉ፡፡ ስለ ፅድቅ ከህብረተሰብ ይገለላሉ፡፡ ስለፅድቅ ጥቅማቸውን ያጣሉ፡፡ ስለፅድቅ በምድር የሚያጡት ነገር ሁሉ ግን እግዚአብሄር መንግስተሰማያትን እንዳዘጋጀላቸው ምልክት ነው፡፡ ስለፅድቅ የሚሰደዱ የሚቀናባቸው ናቸው፡፡ ስለፅድቅ የሚሰደዱ የተመሰገኑ ናቸው፡፡
ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ማቴዎስ 5፡10
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ብፁዕ #ፍቅር #ምህረት #ይቅርታ #እምነት #ፀሎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment