Popular Posts

Monday, August 8, 2016

ለሥጋህ ፈውስ

ስልጣኔና ቴክኖሎጂው እየጨመረ ቢሄድም ሰዎች ስለጤናቸው ከምንም ጊዜ በላይ የሚያስቡበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ በፊት ምግብን እንደ ምግብነቱ የሚመገቡት ቀርቶ ከመመገባቸው በፊት ለጤናዬ ይስማማል ብለው ሁለት ጊዜ ያስባሉ፡፡ አሁን አሁን ምግብ መጣፈጡ ብቻ ሳይሆን ጤነኛ ነው አይደለም ከሰውነቴ ጋር ይስማማል አይስማማም ተብሎም ይጠየቃል ይመረመራል፡፡

በፊት እንዳይራብ ያገኘውን የሚበላው ሰው አሁን ሆዴን በምን አይነት ምግብ ነው የምሞላው ብሎ በደንብ ያስባል፡፡ ሌላ ጊዜ ያመረውንብ የሚበላው ሰው አሁን ምግቤ ስብ እንዳይበዛው ብሎ ይጠነቀቃል፡፡

ያለንን ምድራዊ እውቀት ሁሉ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን እንዴት እንደፈጠረውና ሰውነታችን እንዴት እንደሚሰራ በዘርፉ የተሰማሩትን ሰዎች እውቀት መጠቀም ምክራቸውንም መስማት ይገባል፡፡

ሳይንስም ገና እያጠና እየተመራመረ ስለሆነና ሳይንሲስቶችም እርስ በእርሳቸው እየተከራከሩ በመሆኑ ስለአንዳን ነገር እርግጠኛ መልስ ከሳይንስ መጠበቅ ያዳግታል፡፡ ምክኒያቱም ሳይንሱም በአፅንኦት የሚያስተምረውን ሌላ ጊዜ ሲያፈርሰው ብዙ ጊዜ ተስተውሏል፡፡ 
 
ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የማይለወጠውና ለዘላለም ፀንቶ የሚኖረው የእግዚአብሄር ቃል ስለ ሰውነታችን ፈውስ የሚናገረውን መስማት ወደር የማይገኝለት ጥበብ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ስለ 100% አስተማማኝ መድሃኒት ይናገራል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ምንም ያልተፈለገ ውጤት /side effect/ ስለሌለው መድሃኒትና ፈውስ ይናገራል፡፡ 
 
እግዚአብሄር በሰው ጤንነት ደስ ይሰኛል፡፡ ሰው ሲፈጠር ሙሉ ጤነኛ ተደርጎ ነው በእግዚአብሄር የተፈጠረው፡፡ ሰው ጤንነቱን ያጣው ሃጢያትን በሰራ ጊዜና በእግዚአብሄር ላይ ባመፀ ጊዜ ብቻ ነበር፡፡

እንዲሁም በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ ለስጋችን ፈውስን ይመለሳል፡፡ እግዚአብሄርን መታዘዝ ለስጋችን ፈውስን ያመጣል፡፡ በራስ ማስተዋል አለመደገፍ በሽታን ከስጋችን ያርቃል፡፡
እግዚአዘብሄ የሰውን ሰውነት ንድፍ የነደፈውና የፈጠረው ለክፋት ባለመሆኑ ለሰው ከክፋት መራቅ ለሰውነቱ ጤናን ይመልሳል፡፡ ለእግዚአብሄር አምላክነትና ገዢነት እውቅና መስጠት ለነፍሳችን ሰላም መስጠት ብቻ ሳይሆን ለስጋችን ፈውስን ይሰጣል፡፡ 
 
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ከክፋትም ራቅ፤ ይህም ለሥጋህ ፈውስ ይሆንልሃል፥ ለአጥንትህም ጠገን። ምሳሌ 3፡5-8
 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ 
 
#ፈውስ #እምነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment