Popular Posts

Thursday, August 4, 2016

ስማችሁ በሰማያት ስለ ተጻፈ

ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ። ሉቃስ 10፡20 
 
እግዚአብሄር ለሃጢያታችን መድሃኒት ባዘጋጀው በእየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትና ጌትነት በማመናችን ስማችን በህይወት መዝገብ ላይ ተፅፎአል፡፡ 
 
ስማችን በህይወት መዝገብ ላይ ስለተፃፈ ስንሞት ወይም ነፍሳችን ከስጋችን ሲለይ ከእግዚአብሄር ጋር ለዘላለም እንኖራለን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ እየሱስን የጣሉና ያልተቀበሉ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደተዘጋጀው ወደ እሳት ባህር ይጣላሉ፡፡ ምክኒያቱም በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ ሁሉ ለአሳቹ ለአውሬው ይሰግዳሉ፡፡
 
ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል። ራእይ 13፡8 
 
በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ። ራእይ 20፡15 
 
በምድር ላይ ከምናደርገው ማንኛውም ግኝትና ስኬት በላይ የሚያስደስተው ስማችን በህይወት መዝገብ ላይ ማፃፉና ወደመንግስተ ሰማያት እንደምንገባ ማረጋገጣችን ነው፡፡ 
 
በምድር ላይ ካሉ ደስታዎች ሁሉ ይልቅ ዘላቂው ደስታ ከእግዚአብሄር ጋር ለዘላለም እንድንኖር እግዚአብሄር እኛን ልጅ አድርጎ መቀበሉ ነው፡፡ በምድር ላይ ከምናገኛቸው ደስታዎች ሁሉ የሚበልጠው ከዚህ ጊዜያዊ ስጋ ስንለይ ዘላለማችንን የምናሳልፈው ከእግዚአብሄ ጋር መሆኑን ማወቃችን ነው፡፡ 
 
ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ። ሉቃስ 10፡20 
 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ 
 
#መንግስተሰማያት #ዘላለም #ስም #የህይወትመዝገብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment