Popular Posts

Tuesday, August 16, 2016

ሃይል አያስመካም ማስተዋል እንጂ

ሁሉም ሰው በምድር ላይ እንዲከናወን ይፈልጋል ከክንውንም መጉደል የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ ሰውም የክንውን መንገዶች የሚባሉትን ሁሉ ማጥናት መከተል ይፈልጋል፡፡
በዚህ ረገድ ሰዎች እነዚህ የህይወት ቁልፍ ናቸው ብለው ካለማወቅ የሚሳሳቱባቸው ሶስት ነገሮች አሉ፡፡
በየዘመኑ የኖሩ ሰዎች የህይወት ዘመናቸውን እነዚህን በመፈለግ ቢፈጁም በኋላ ግን የጠበቁት ስለማይሆን ያዝናሉ ይሰናከላሉ፡፡ ለማይጠቅም ለከንቱ ነገር ጊዜያቸውን ስለፈጁ ይፀፀታሉ፡፡ ስለዚህ ነው መፅሃፍ ስለ እነዚህ ሰዎች በስህተት ስለሚመኩባቸው ሶስት ነገሮች በየጊዜው በተለያለ መልኩ የሚናገረው፡፡ በመፅሃፍ ቅዱስ ሰው በጥበቡ በሃይሉና በባለጠግነቱ እንዳይመካ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃል፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ኤርሚያስ 9፡23
እግዚአብሄር እንዲህ እያለ ነው ፡፡ የሰው ጥበብ እንደ ህይወት ቁልፍ የሚያስመካ ነገር አይደለም፡፡ የሰው ጥበብ እንደ ስኬት ምንጭ ወሳኝ አይደለም፡፡ ጥበብ የሚያደርጋቸው ውስን ነገሮች አሉ ነገር ግን የሰው ጥበብ የህይወት መንገድ አይደለም፡፡
በሌላ አነጋገር ጥበብ የሌለው ሰው ከህይወት መንገድ እንደጎደለ ሊሰማው አያስፈልግም፡፡ ጥበብ የሌለው ሰው የህይወት ቁልፉን እንዳጣ አይዋረድ፡፡ ጥበብ የሌለው ሰው ህይወት እንደጎደለው አይሰማው፡፡ ጥበብ ጉድለት ምንም ችግር የለውም እያለ ነው፡፡
ሃያልም በሃይሉ አይመካ ማለት ሃያል በሃይሉ ምንም አያመጣም ማለት ነው፡፡ ሃያል ሃይሉ አያስጥለውም ማለት ነው፡፡ ሃያል ሃይሉ በር አይከፍትለትም ማለት ነው፡፡ ሰው በሃይሉ ጠብ የሚል ነገር የለም ማለት ነው፡፡ ሰው በሃይሉ መመካቱ አያዋጣውም፡፡
በሌላ አነጋገር ደካማው ከህይወት መንገድ ተጥያለሁ አይበል፡፡ ደካማው በድካሙ ዝቅ ዝቅ አይበል፡፡ ደካማው በድካሙ አይዘን ማለቱ ነው፡፡ ደካማው ድካ ብቻ ከህየወት ሩጫ ሊያሰወጣው የሚችል በቂ ምክኒያት አይደለም ማለት ነው፡፡
እንዲሁም ባለጠጋም በብልጥግናው አይመካ ማለት የህይወት ስኬት ቁልፍ በባለጠግነት ውስጥ አይደለም ማለት ነው፡፡ ባለጠጋ ስለሆነ ብቻ ህይወትን ያገኘ አይምሰለው ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት የሚያስመካ ምንም ነገር የለውም ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማድረግ የማይችላቸው በጣም ብዙ ነገሮች አሉ እያለ ነው፡፡
የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ አላቸው። ሉቃስ 12፡15
እንዲሁም ደግሞ ደሃ የህይወት ቁልፉን እንዳጣ አይሰማው ማለት ነው፡፡ ደሃ ምንም እንደጎደለበት አይሰማው፡፡ ድሃ በድህነቱ አይዋረድ፡፡
ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 9፡23-24
የህይወት ቁልፍ ሃይል ሃብትና ጥበብ ውስጥ አይደለም፡፡ የስኬት ቁልፍ ያለው እግዚአብሄር እጅ ነው፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ የሰውን ፊት አይቶ አያዳላም፡፡ እግዚአብሄር የሰውን ሃያልነትና ድካም ፣ የሰውን ባለጠግነትና ድህነት ፣ የሰውን ጥበብና የጥበብ ጉድለት ተከትሎ ምንም የሚሰራው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ምድርን የሚያስተዳድረው ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በማድረግ ነው፡፡ በጥበቡ የሚመካ ሰው ሞኝ ነው፡፡ በሃይሉ የሚመካ ሰው ደካማ ነው ፡፡
በባለጠግነቱ የሚመካ ሰው ድሃ ነው፡፡ ስለዚህ የሰው ስኬት ምንጩ በምድር እንደሌለ የሰው ስኬት ምንጩ እግዚአብሄር እጅ እንዳለ የተረዳ ሰው ይህ መረዳቱ ሊያስፈነድቀውና ሊያስመካው ይችላል፡፡ ምክኒያቱም ሊመኩበት የሚገባ እግዚአብሄ ብቻ ነውና፡፡
በእግዚአብሄር ብቻ መመካት እውነተኛ ባለጠግነት ነው ፣ በእግዚአብሄር መመካት እውነተኛ ሃያልነት ነው ፣ እውነተኛ ጠቢብነት በእግዚአብሄር መመካት ነው፡፡
የሚመካ በእግዚአብሄር ይመካ !
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
#የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #መመካት #ብርታት #እምነት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment