በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፡፡ ምሳሌ 3፡5
ህይወት የእግዚአብሄር ውድ ስጦታ ነው፡፡ ይህን ስጦታ በሚገባ መያዝና መጠቀም ማስተዋል ይጠይቃል፡፡ የህይወትን
ስጦታ በሚገባ ለመጠቀም ወደ ሰጭው መመለስና ለምን እንደሰጠንና ምን እንድናደርግበት እንደሰጠን መረዳት ይጠይቃል፡፡
በሌላ አነጋገር በምድር ላይ ለእግዚአብሄር ክብር ለመኖር ሁልጊዜ በእግዚአብሄር ምሪት ላይ መደገፍ ይጠበቅብናል፡፡
የእግዚአብሄርን ስጦታ ህይወትን በራስህ ማስተዋል አትኖረውም፡፡ የእግዚአብሄርን የህይወት ስጦታ በእግዚአብሄር እውቀትና ምሪት መጠቀም ይጠይቃል፡፡
ሁል ጊዜ በራሳችን እውቀትና ማስተዋል ነገሮችን ለማድረግ እንፈተናለን፡፡ ነገር ግን የራሳችን ማስተዋል ያስተናል እንጂ የትም አያደርሰንም፡፡
አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር፦ ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው። ኢሳያስ 55፡8-9
በእግዚአብሄር የምትታመነውና የምትደገፈው ለእግዚአብሄር አዋቂነትና ፍፁም መሪነትና እውቅና በመስጠት ነው፡፡ ይህን በማለት ለእግዚአብሄር እውቅና ልንሰጥ ይገባናል፡፡
• እኔ ከመፈጠሬ በፊት ለእኔ ያቀድከው ሃሳብ አለ
• የእኔ የህይወት እቅድና ንድፍ በአንተ ዘንድ አለ
• እኔ ለራሴ ከማውቀው በላይ አንተ ለእኔ ታውቃለህ
• አንተ ለእኔ ያለህ አላማ የፍቅር አላማ ነው
• አንተ ለእኔ የምታስበው ሃሳብ መልካም ብቻ ነው
በማለት ይህንን እግዚአብሄር ለህይወታችን ያለውን ሃሳብ ከእግዚአብሄር መፈለግና መከተል መንገዳችን እንዲቃና ያደርጋል፡፡
ምሳሌ 3፡6 በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።
ለተጨማሪ ፅሁፎች
I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና . . . ማቴዎስ 28፡18 በመጀመሪያ ሰው ከሙሉ ስልጣን ጋር ተፈጥሮ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ ...
-
እግዚአብሄር የፈጠረን በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ የእግዚአብሄር መልክ ከሰው ውስጥ የጠፋው ሰው በሃጢያት ወደቀበት ጊዜ ነው፡፡ ኢየሱስ ወደ ምድር መጥቶ የሃጢያታችንን ሁሉ እዳ የከፈለው ወደ እግዚአብሄር መልክና አምሳል...
-
እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ እግዚአብሄር በስጋ አይን አይታይም፡፡ እግዚአብሄር ምን እንደሚሰራ ለማየትና ከእርሱ ጋር ለመስማማትና ለመተባበር የመንፈስ አይን ይጠይቃል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር በሚገባ ለመኖር በተፈጥሮአዊ አይ...
-
We want God to use us mightily. We ask God “use me and I will do whatever it takes”. When the time to pay the price that isn’t expected...
-
ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው። ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው። በጽዮን ተራሮች ...
-
የእግዚአብሄር ስራ የሚሰራው በመንፈስ ነው፡፡ በእግዚአብሄር መንግስት እውነተኛ አገልግሎት ለማገልገል መቀጣጠሉና ግለቱ ወሳኝ ነው፡፡ ሰው ሁሉ ነገር ቢኖረው ነገር ግን ምንም መነሳሳትና መቀጣጠል ከ...
-
እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥...
-
እግዚአብሄር እንድትሰሩ የሰጣችሁን ስራ ለመስራት ምንም ሃይል አይጎድልባችሁም፡፡ እግዚአብሄር የጠራችሁን ለማድረግ ምንም አታጡም፡፡ እግዚአብሄር ያላችሁ ቦታ ለመድረስ ምንም አቅም አይጎድልባችሁም፡፡ እግዚአብሄር የጠ...
-
አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19 እንዳላችሁ ንግድ ብዛት፣ እንዳላችሁ የባንክ ሂሳብ ፣ እንዳላችሁ የቤተሰብ ውርስ ፣ እንዳላችሁ ን...
No comments:
Post a Comment