Popular Posts

Thursday, June 23, 2016

የሚበልጥ ምርጫ

ዛሬ ለእንግሊዞች የምርጫ ቀን ነው፡፡ ምርጫ ደግሞ እድልን ይወስናል፡፡
 
እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ለመቆየትና ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት ህዝቡ ምርጫን ያደርጋል፡፡ ከህብረቱ መውጣት የሚያስከትለውን ጉዳትና በህብረቱ መቆየት ያለውን ጥቅም በማስረዳት የህብረቱ ደጋፊዎች አብዛኛው ሰው ህብረቱን እንዲመርጡ ይቀሰቅሳሉ፡፡
 
እንግሊዝ ከህብረቱ መውጣት ይሻላታል የሚሉ ወገኖችም እንዲሁ ከህብረቱ መለየት የሚጠቅመውን ጥቅምና በህብረቱ መቆየት የሚጎዳውን ጉዳት በመዘርዘር ከህብረቱ መውጣትን ብዙዎች እንዲመርጡ ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል፡፡
 
ከህብረቱ መውጣትምን ሆነ በህብረቱ መቆየት ጥቅምም ጉዳትም ይኖረዋል፡፡ ይህ የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡
 
ከእነዚህ ሁሉ እጅግ የበለጠ ጥቅም ያለውና ካልመረጥነው እጅግ የከፋ ጉዳት ያለው በህይወት ዘመናችን መምረጥ ያለብን ወሳኝ ምርጫ ደግሞ አለ፡፡ ይህ ምርጫ የምድር ኢኮኖሚያችንን ጤናችንንና ደህንነታችንን ብቻ ሳይሆን የዘላለም እጣ ፈንታችንን ነው የሚወስነው ፡፡
 
እግዚአብሄር እየሱስን ወደ ምድር ሲልከው ለሃጢያታችን እንዲሞትና በመስቀል ላይ የሃጢያታችንን እዳ እንዲከፍል ነው፡፡
 
ይህንን እየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለውን የሃጢያት ዋጋ ለእኔ ነው ብሎ የሚቀበልና እየሱስን የሚመርጥ የዘላለም ህይወት ያገኛል፡፡ አይ የሚልና የእግዚአብሄርን ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ የማይቀበል ለዘለአለም ከእግዚአብሄር በመለየት የዘላለም ፍርድ ያገኛል ፡፡
 
በምድር ላይ እየሱስን የሚመርጡና የእግዚአብሄር ልጅነትን ስልጣን የሚቀበሉ አሉ፡፡ በምድር ላይ እስከመጨረሻው እየሱስን የማይመርጡ አሉ፡፡
 
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
 
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 3፡16
 
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36


No comments:

Post a Comment