I am a born again christian passionate to teach the word of God in simplicity.
Popular Posts
-
So if the Son sets you free, you will be free indeed. John 8:36 Mankind isn’t designed for any kinds of bondage. God created ma...
-
ከከንቱ ኑሮአችንም የተገዛነው እና የተዋጀነው በክርስቶስ ደም ነው፡፡ ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክ...
-
ኢየሱስ ወደምድር የመጣው በስጋ ነው፡፡ ኢየሱስ የመጣው ከሰው ልጅ ተወልዶ ሰው ሆኖ ነው፡፡ ኢየሱስ ሰው ሆኖ የመጣው በሰው የተሰራውን ሃጢያት በሰውነት ለመክፈል ነው፡፡ እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍ...
-
በምድር ላይ ተቋቁሞ ለማለፍ እንዲሁም ከማንኛውንም ክፋት ለመዳን እግዚአብሄርን መፍራት በጣም ወሳኝ ነው፡፡ እግዚአብሄርን መፍራት ማለት ደግሞ እግዚአብሄርን እንደ እግዚአብሄርነቱ መጠን ማክበር እና መስማት ማለት ነ...
-
የዲያቢሎስ አላማ አንድና አንድ ነው፡፡ ዲያቢሎስ ከመጣ ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ለሌላ ነገር አይመጣም፡፡ ዲያቢሎስንብ የመጋዣው መንገድ ደግሞ በእግዚአብሄር ላይ ማመፅ ወደ እግዚአብሄር...
-
ክርስቲያናዊ ደስታን አፈላለግ በሚቀጥሉት አምስት እምነቶች ላይ የተገነባ የህይወት መረዳት ነው፡፡ l. ደስተኛ ለመሆን መጓጓት አለም አቀፋዊ ሁለንተናዊ የሰዎች ምኞት ነው፡፡ ደስተኛ ለመሆ...
-
በአዳም ምክኒያት የሰው ልጅ ሁሉ በሃጢያት እስራት ውስጥ ወድቆዋል፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ለመኖር ንስሃ መግባት አለበት፡፡ የአለም የአሰራር ስርአትና የእግዚአብሄር መንግስት አሰራር ፍፁም የተለያዩ ናቸው፡፡...
-
ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ዮሃንስ 14፡27 ነገር ግን እኛ ነን ሰላማችንን የመጠበቅ ሃላፊነት ያለብን ፡፡ ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ እኛ ይ...
-
ፍቅር አስደናቂ ነው፡፡ በተለይ ፍቅር ሁሉን ያምናል የሚለውን ቃል ሳሰላስል ነበር ያመሸሁት፡፡ ይህን ቃል ሳሰላስል ጌታ የሰጠኝን መረዳት አብሬያችሁ ልካፈል ወደድኩ፡፡ ፍቅር ሁሉን ያምናል፡፡ 1ኛ ቆሮንጦስ ...
-
የፈጠረን እግዚአብሄር ሁለንተናችንን ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር በውጫዊ ነገራችን አይወሰድም፡፡ እግዚአብሄር ፊትን አያየም፡፡ እግዚአብሄር የፊትን መልክ አይቶ አይሳብም፡፡ እግዚአብሄር ቁመናችንን አይቶ አይደነቅም፡፡...
Friday, June 3, 2016
መዝሙርን ዘፈን ያላደረገው
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዘፈን ሃጢያት ነው ? የሚል ጥያቄ ተነስቶ ብዙዋቻችንን ሲያነጋግር ቆይቶዋል፡፡ እኔም በልቤ ያለውን የሚሰማኝን ዘፈን ሃጢያት ነው በሚል ርእስ ፅሁፍን ፅፌ ነበር፡፡
እግዚአብሄር መዝሙርን እንደሚፈልግ ዘፈንን ግን እንደማይፈልግ እንዲያውም ዘፋኝነት የስጋ ስራ እንደሆነ እነዚህን የሚያደርጉም የእግዚአብሄርን መንግስት እንደማይወርሱ መፅሃፍ ስለዘፈን ጎጂነትር በአፅንኦት ይናገራል፡፡
እግዚአብሄር ዘፈንን ለምን ጠላ መዝሙርንስ ለምን ወደደ? የሚለውን ለመመለስ መዝሙር ከዘፈን የሚለይበትን ነገሮች ማወቅ ግድ ይላል፡፡
መዝሙር እንደ ማንኛውም ዘፈን በግጥም በዜማ የሚሆን እንጉርጉሮ ቢሆንም እንዲሁም መዝሙርንም ዘፈንም የምንጫወትበት መሳሪያ ተመሳሳይ ቢሆንም መዝሙርን ዘፈን የማያደርገው ብዙ ወሳኝ መሰረታዊ ነገሮች አሉት፡፡
መዝሙርን ዘፈን ያላደረገው
1. የመዝሙር አላማ ሰዎች በእግዚአብሄር መልክና አምሳል የተፈጠሩ ክቡራን እንደሆኑና ሰይጣንን ሰምተው በሃጢያት እንዳይዋረዱና ከንቱ እንዳይሆኑ እግዚአብሄር እንደ ፈጠራቸው የክብር ደረጃ እንዲኖሩና ማስተማር ነው፡፡
2. የመዝሙር አላማ ሰዎች እግዚአብሄር በክርስቶስ የከፈለላቸውን የሃጢያት ዋጋ እንዲረዱና ክርስቶስ ለእነርሱ እንደሞተላቸው እነርሱ ደግሞ ለሃጢያት ሞተው ለክርስቶስ እንዲኖሩ የሚያበረታታ ነው፡፡
3. የመዝሙር አላማ ሰዎች የህይወት ጠላት የሆነውን ዲያቢሎስን እና ስራውን ከህይወታቸው እንዲክዱ ልቅነትንና ሃጢያትን እንዲፀየፉ ራስን እንዲገዙ ማበረታታት ነው፡፡
4. የመዝሙር አላማ ሰዎች በጊዜያዊ የአለም ደስታ ዘላለማዊ ህይወታቸውን እንዳያጡ የዘላለም ህይወታቸውን አጥብቀው እንዲይዙ ለማበረታታት የታለመ ነው፡፡
5. የመዝሙር አላማ ሰዎች በምድር ላይ ጊዜያዊ ተላላፊ ምፅአተኛ እንደሆኑ አውቀው በአለም ጉድፍ ራሳቸውን እንዲጠብቁ መምከር ነው፡፡
ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤1ኛ ጴጥሮስ 2፡11
6. መዝሙር ሰዎች ለፈጠራቸው ባለቤታቸው ለሆነውና ዘወትር ክብር ለሚገባው ለእግዚአብሄር ክብር እንዲሰጡ የሚመራ ነው፡፡
7. መዝሙር እግዚአብሄርን ከምንም በላይ እንዲያከብሩና እርሱን ለማስደሰት እንዲኖሩ የስጋ ምኞታቸውንና የነፍሳቸውን ክፉ ፍላጎት እንቢ እንዲሉ እግዚአብሄርን ለማሳየት የሚዘመር ነው፡፡
8. መዝሙር እንካ በእንካ ያልሆነን ከራስ ወዳድነት የፀዳ ልጁን እየሱስን ለእኛ በመስጠት ያሳየውን የእግዚአብሄርን እውነተኛ ፍቅር የሚገልፅ ነው፡፡
9. እውነተኛ ሰላም የሚገኘው ለእግዚአብሄር አምላክነት ስንገዛና እግዚአብሄ የፈጠረንን አላማ ስንከተል ብቻ እንጂ በተለያየ ቁሳቁስና ልምምድ የማይመጣ መሆኑን የሚያሳይ መዝሙር ነው፡፡
https://www.facebook.com/abiy.wakuma
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment